ልጄ ሆይ፥ አሁን እንግዲህ ስማኝ፥ ወደ አፌ ቃል አድምጥ።
ልጆቼ ሆይ፤ አሁንም አድምጡኝ፤ የምለውንም ልብ ብላችሁ ስሙኝ።
ልጆቼ ሆይ፥ አሁን እንግዲህ ስሙኝ የአፌንም ቃል አድምጡ።
እንግዲህ ልጄ ሆይ! አድምጠኝ፤ የምልህንም በጥንቃቄ ስማ፤
ስለ በጎ ፋንታ ክፉን መለሱልኝ፥ ሰውነቴንም ልጆችን አሳጡአት።
ዐዋቂ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይሰማል፤ የማይሰማ ልጅ ግን ይጠፋል።
ልጆች ሆይ፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፤
አሁንም ልጄ ሆይ፥ ስማኝ፥ ቃሌንም የተናቀ አታድርግ
ልጆች፥ እንደ ገና የምጨነቅላችሁ ክርስቶስ በልባችሁ እስኪሣልባችሁ ድረስ ነው።
ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።