ምሳሌ 6:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቍስልንና ውርደትን ያገኛል፥ ስድቡም ለዘለዓለም አይደመሰስም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መደብደብና ውርደት ዕጣው ነው፤ ኀፍረቱም ከቶ አይወገድም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁስልንና ውርደትን ያገኛል፥ ስድቡም አይደመሰስም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውርደትና ድብደባ ይደርስበታል፤ ሁልጊዜም እንደ ተዋረደ ይኖራል። |
ከኬጥያዊው ከኦርዮ ነገር በቀር ዳዊት በዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አድርጎ ነበርና፥ ካዘዘውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላለም ነበርና።
የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን በዚህ ነገር ኀጢአት አድርጎ የለምን? በብዙ አሕዛብም መካከል እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ አልነበረም፤ በአምላኩም ዘንድ የተወደደ ነበረ፤ እግዚአብሔርም በእስራኤል ሁሉ ላይ አንግሦት ነበር፤ እርሱንም እንኳ እንግዶች ሴቶች አሳቱት።
እኔስ በእግዚአብሔር ቤት እንደ ለመለመ እንደ ወይራ ዛፍ ነኝ፤ ለዓለምና ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ምሕረት ታመንሁ።