አሁንም ልጄ ሆይ፥ ስማኝ፥ ቃሌንም የተናቀ አታድርግ
እንግዲህ፣ ልጆቼ ሆይ፤ አድምጡኝ፤ ከምነግራችሁ ቃል ፈቀቅ አትበሉ።
አሁንም ልጆቼ ሆይ፥ ስሙኝ፥ ከአፌም ቃል አትራቁ።
ልጄ ሆይ! አድምጠኝ፤ እኔም ከምነግርህ ትምህርት አትራቅ።
ልጄ ሆይ፥ ቸል አትበል ዐሳቤንና ምክሬን ጠብቅ፤
ልጆች ሆይ፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፤
ምንጮችህ እንዳይደርቁ፥ በልብህ ጠብቃቸው።
ልጄ ሆይ፥ አሁን እንግዲህ ስማኝ፥ ወደ አፌ ቃል አድምጥ።
ለሚናገረው እንቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነርሱ በደብረ ሲና የተገለጠላቸውን እንቢ ስለ አሉት ካልዳኑ፥ ከሰማይ ከመጣው ፊታችንን ብንመልስ እኛማ እንዴታ?