ምሳሌ 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጥበብን መንገዶች አስተምርሃለሁና፤ በቀናች ጎዳና መራሁህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጥበብ ጐዳና አስተምርሃለሁ፤ ቀጥተኛውንም መንገድ አሳይሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጥበብን መንገድ አስተማርሁህ፥ በቀናች ጎዳና መራሁህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጥበብን መንገድ አሳየሁህ፤ በቀና መንገድም መራሁህ። |
እንዲህም አለው፥ “ሽንገላንና ክፋትን ሁሉ የተመላህ፥ የሰይጣን ልጅ፥ የጽድቅ ሁሉ ጠላት ሆይ፥ የቀናውን የእግዚአብሔርን መንገድ ማጣመምህን ትተው ዘንድ እንቢ አልህን?
እነሆ፥ እናንተ ገብታችሁ በምትወርሱአት ምድር ውስጥ እንዲህ ታደርጉ ዘንድ አምላኬ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ ሥርዐትና ፍርድን አሳየኋችሁ።