ምሳሌ 24:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ከሰው ሁሉ ይልቅ ሰነፍ ነኝና፥ የሰውም ማስተዋል በእኔ ላይ አልነበረምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በእኔ ላይ እንደ ሠራብኝ እሠራለታለሁ፤ ስለ አድራጎቱም የእጁን እመልስለታለሁ” አትበል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዳደረገብኝ እንዲሁ አደርግበታለሁ፥ እንደ ሥራውም እበቀለዋለሁ አትበል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰው ክፉ ነገር በሚያደርግብኝ መጠን እኔም ክፉ ነገር አደርግበታለሁ! የበቀል ብድራቴንም እመልሳለሁ!” አትበል። |
ከይሁዳም ሰዎች ሦስት ሺህ የሚያህሉ በኢጣም ዓለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሶምሶንን፥ “ገዢዎቻችን ፍልስጥኤማውያን እንደሆኑ አታውቅምን? ያደረግህብን ይህ ምንድን ነው?” አሉት። ሶምሶንም፥ “እንዳደረጉባችሁ እንዲሁ አደረግሁባቸው” አላቸው።