እንዲሁም ጥበብን በሰውነትህ ተማር፥ ብታገኛት ፍጻሜህ መልካም ይሆናል፥ ተስፋህም አይጠፋም።
ጥበብም ለነፍስህ እንደዚሁ ጣፋጭ እንደ ሆነች ዕወቅ፤ ብታገኛት ለነገ አለኝታ ይኖርሃል፤ ተስፋህም ከንቱ አይሆንም።
ጥበብም ለነፍስህ እንዲሁ እንደሚሆን እወቅ፥ ብታገኘውም ፍጻሜህ መልካም ይሆናል፥ ተስፋህም አይጠፋም።
ጥበብም ለነፍስህ መልካም መሆኑን ዕወቅ፤ ጥበብን ብታገኝ የወደፊት ኑሮህ የተቃና ይሆናል፤ ተስፋህም አያቋርጥም።
ያማረ ቃል የማር ወለላ ነው፤ ጣፋጭነቱም የነፍስ መድኀኒት ነው።
ጥበብ ወደ ልብህ በመጣች ጊዜ፥ ዕውቀትም ለነፍስህ መልካምና ክብር በሆነች ጊዜ፥
እነርሱን በልብህ ብትጠብቅ፥ በከንፈሮችህ በአንድነት ደስ ያሰኙሃል።
ብትጠብቃቸው ዘመድ ይሆኑሃል፥ ተስፋህም አትጠፋም።
ቃልህ ተገኝቶአል፤ እኔም በልችዋለሁ፤ አቤቱ! የሠራዊት አምላክ ሆይ! ቃልህን የከዱ ሰዎችን አጥፋቸው፤ ስምህ በእኔ ላይ ተጠርትዋልና፥ ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ።
ኢየሱስም “ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፤ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፤ መጥተህም ተከተለኝ፤” አለው።
ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል።