ምሳሌ 23:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ጠቢብም ሁን፥ የልብህንም ዐሳብ አቅና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጄ ሆይ አድምጥ፤ ጠቢብም ሁን፤ ልብህም ከትክክለኛው መንገድ አይውጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ጠቢብም ሁን፥ ልብህንም በቀናው መንገድ ምራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጄ ሆይ! አድምጥ፤ ብልኅም ሁን፥ ከእግዚአብሔርም መንገድ ፈቀቅ አትበል፤ |
የከተማዉንም ሰዎች፦ ‘ይህ ልጃችን ትዕቢተኛና ዐመፀኛ ነው፥ ቃላችንንም አይሰማም፤ ስስታምና ሰካራም ነው’ ይበሉአቸው።
“ለራስህ ዕወቅ፤ ሰውነትህን ፈጽመህ ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ይህን ሁሉ ነገር አትርሳ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ከልቡናህ አይውጣ፤ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህም አስተምራቸው።