ልብህን ለተግሣጽ ስጥ፥ ጆሮህንም ለዕውቀት ቃል አዘጋጅ።
ልብህን ለምክር፣ ጆሮህንም ለዕውቀት ቃል ስጥ።
ልብህን ለምክር ስጥ፥ ጆሮህንም እንዲሁ ለእውቀት ቃላት።
አእምሮህን በትምህርት ላይ፥ ጆሮህንም ዕውቀትን በመስማት ላይ አውላቸው።
ለመስማት ጆሮህን ወደ ጠቢባን ቃል አዘንብል፥ የእኔንም ቃል ስማ፥ መልካምንም ታውቅ ዘንድ ልብህን አቅርብ።
ታዳጊአቸው እግዚአብሔር ጽኑ ነውና፥ እርሱም ፍርዳቸውን ከአንተ ጋር ይፋረዳልና።
ሕፃናትን ከመቅጣት ቸል አትበል፥ በበትር ብትመታቸው አይሞቱምና።
ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ጠቢብም ሁን፥ የልብህንም ዐሳብ አቅና።
ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፤ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፤ ቃልህንም ይሰማሉ፤ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ሐሰት ነገር አለና፥ ልባቸውም ጣዖታትን ይከተላልና።
እርሱም “ስለዚህ የመንግሥተ ሰማያት ደቀ መዝሙር የሆነ ጻፊ ሁሉ ከመዝገቡ አዲሱንና አሮጌውን የሚያወጣ ባለቤትን ይመስላል፤” አላቸው።