ታዳጊአቸው እግዚአብሔር ጽኑ ነውና፥ እርሱም ፍርዳቸውን ከአንተ ጋር ይፋረዳልና።
ታዳጊያቸው ብርቱ ነውና፤ እርሱ ይፋረድላቸዋል።
ታዳጊአቸው ኃያል ነውና፥ እርሱም ፍርዳቸውን ከአንተ ጋር ይፋረዳልና።
እግዚአብሔር ጽኑ መከታቸው ስለ ሆነ ለእነርሱ ይከራከርላቸዋል።
እኔን ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥ በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንዲቆም፥
እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ፥ ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።
አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ፥ የሚሹህ በእኔ አይፈሩ፤ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ተስፋ የሚያደርጉህ በእኔ አይነወሩ።
እግዚአብሔር ፍርዱን ይፈርድለታልና። አንተም ነፍስህን በሰላም ታድናለህ።
ልብህን ለተግሣጽ ስጥ፥ ጆሮህንም ለዕውቀት ቃል አዘጋጅ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ የሚገፋሽን እፈርድበታለሁ፤ በቀልሽንም እበቀልልሻለሁ፤ ባሕርዋንም ድርቅ አደርገዋለሁ፤ ምንጭዋንም አደርቃለሁ።
“በመጻተኛ፥ በድሃ-አደጉም፥ በመበለቲቱም ላይ ፍርድን የሚያጣምም ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።