ባለ ጠጋና ድሃ በአንድነት ተገናኙ፤ ሁለቱንም እግዚአብሔር ፈጠራቸው።
ባለጠጋና ድኻ የሚጋሩት ነገር፣ እግዚአብሔር የሁላቸውም ፈጣሪ መሆኑ ነው።
ሀብታምና ድሀ ይገናኛሉ፥ ሁለቱንም የፈጠራቸው ጌታ ነው።
ሀብታምንም ሆነ ድኻን የፈጠራቸው እግዚአብሔር ስለ ሆነ ሁለቱም በዚህ አንድ ናቸው።
እኔን በማኅፀን የፈጠረ እነርሱንስ የፈጠረ አይደለምን? በማኅፀንስ ውስጥ የሠራን አንድ አይደለምን?
እርሱ ግን የክቡርን ሰው ፊት አያፍርም። ለታላቁም ክብር መስጠትን አያውቅም፥ ከፊታቸውም አይሸሽም።
ድሃን የሚያስጨንቅ ፈጣሪውን ያስቈጣዋል፤ ፈጣሪውን የሚያከብር ግን ለድሃ ምሕረትን ያደርጋል።
ዐይን እጅን፥ “አልፈልግሽም” ልትላት አትችልም፤ ራስም፥ “እግሮችን አልፈልጋችሁም” ልትላቸው አትችልም።
እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፤ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፤ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል።