ምሳሌ 22:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለማወቅ የጐልማሳን ልብ ከፍ ከፍ አደረገች፤ በትርና ተግሣጽ ከእርሱ ርቀዋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቂልነት በሕፃን ልብ ታስሯል፤ የተግሣጽ በትር ግን ከርሱ ያርቅለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቂልነት በልጅ ልብ ውስጥ ተተብትቧል፥ የተግሣጽ በትር ግን ነፃ ያደርገዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በልጅ ልብ ውስጥ ሞኝነት አለ፤ የተግሣጽ በትር ግን ከእርሱ ያስወግደዋል። |
ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያፈርስሃል፤ ከቤትህም ይነቅልሃል፥ ያፈልስሃልም፥ ሥርህንም ከሕያዋን ምድር።
እኛ ሁላችን ቀድሞ እንደ ሥጋችን ምኞት ኖርን፤ የሥጋችንንም ፈቃድና ያሰብነውን አደረግን፤ እንደ ሌሎች ኃጥአንም ሁሉ የጥፋት ልጆች ሆንን።