እግዚአብሔር የልብን የውሀት ይወድዳል። ንጹሓንም ሁሉ በእርሱ ዘንድ የተመረጡ ናቸው። ንጉሥ በከንፈሩ ይገዛል።
የልብ ንጽሕናን ለሚወድድና ንግግሩም ሞገስ ላለው ሰው፣ ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል።
የልብን ንጽሕናን የሚወድና ንግግሩ ለዛ ያለው ሰው፥ ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል።
የልብ ንጽሕናንና መልካም ንግግርን የሚወድ ሰው በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ይሆናል።
የናታንም ልጅ ኦርኒያ የሹሞች አለቃ ነበረ፤ የናታንም ልጅ ዘባት የንጉሡ አማካሪና ወዳጅ ነበረ፤
እንደ ሜዳ አህያ ሆንኹ፤ ሌሊት በወና ቤት እንዳለ እንደ ጕጕት ሆንሁ።
አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፤ ፍለጋህንም አስተምረኝ።
ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢፈልሱ አንፈራም።
አስተዋይ መልእክተኛ በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ነው፤ በመልካም ጠባዩም ውርደትን ከራሱ ያርቃል።
የእውነት ከንፈር በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ነው፥ ቅን ነገርንም ይወድዳል።
የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ ኃጥእ ግን የጥበብን ቃል ይንቃል።
የጠቢብ ሰው የአፉ ቃል ሞገስ ናት፤ የሰነፍ ከንፈሮች ግን ራሱን ይውጡታል።
ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፤እግዚአብሔርን ያዩታልና።
ሁሉም የንግግሩን መከናወን መሰከሩለት፤ የአንደበቱንም ቅልጥፍና እያደነቁ፥ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” ይሉ ነበር።