ለማያውቀው ከተዋሰ ሰው ልብሱን ውሰድ፥ ለእንግዳ የተዋሰውንም እርሱን አግተው።
ለማይታወቅ ሰው ዋስ የሆነውን ልብሱን ግፈፈው፤ ለባዕድ ሴት የተዋሰውን በቃሉ ዐግተው።
ማንም ሰው ለእንግዳ ሰው ከተዋሰ፥ ልብሱን ውሰድ፤ ለማይታወቀው ሰው መያዣ እንዲሆን አንተ ዘንድ አስቀምጠው።
ክፉ ሰው ከጻድቅ ጋር በተቀላቀለ ጊዜ ይከፋል፥ የሰላም ድምፅንም ይጠላል።
ከቀናች መንገድ እንዳያርቁህ፥ እውነትንም ከማወቅ የተለየህ እንዳያደርጉህ፤ ልጄ ሆይ፥ በሕፃንነትህ ትምህርትን የምታስተው፥ ክፉ ምክር አታግኝህ፤
ወርቅና ብዙ ቀይ ዕንቍ ይገኛል፤ የዕውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።
የሐሰት እንጀራ ለሰው የጣፈጠ ነው፤ ከዚህ በኋላ ግን አፉ ጭንጫ ይሞላል።
አመንዝራ ሴት የተነደለች ማድጋ ናት፥ ሌላዪቱም ሴት የጠበበች ጕድጓድ ናት።
ከአመንዝራ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና፥ ወደ አመንዝራ ሴት አትመልከት፥ ለጊዜው ጕሮሮህን ያጣፍጣል፥
ልጄ ሆይ፥ ለወዳጅህ ዋስ ብትሆን፥ እጅህን ለባላጋራህ ትሰጣለህ፤
የምንዝር ጌጥ ያላት የጐልማሶችን ልብ እንዲሰቀል የምታደርግ ሴት ያንጊዜ ትገናኘዋለች። እርስዋ የምትበርር መዳራትንም የምትወድ ናት።
ከባዕድና ከክፉ ሴት ዋዛ ነገርንም ከምታመጣብህ ትጠብቅህ ዘንድ።