ምሳሌ 20:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለት ዐይነት ሚዛንና ሁለት ዐይነት መስፈሪያ፥ ሁለቱ በእግዚአብሔር ፊት ርኩሳን ናቸው። የሚሠራቸውም በሥራው ይሰነካከላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለት ዐይነት ሚዛን፣ ሁለት ዐይነት መስፈሪያ፣ ሁለቱንም እግዚአብሔር ይጸየፋቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለት ዓይነት ሚዛንና ሁለት ዓይነት መስፈሪያ፥ ሁለቱ በጌታ ፊት ርኩሳን ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በሐሰተኛ ሚዛንና ትክክል ባልሆነ መስፈሪያ የሚጠቀሙ ሰዎችን ይጠላል። |
የእውነትም ሚዛን፥ የእውነትም መመዘኛ፥ የእውነትም የፈሳሽ መስፈሪያ ይሁንላችሁ፤ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እኔ ነኝ።
ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”