ምሳሌ 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፥ አምላክን ማወቅንም ታገኛለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ፈሪሀ እግዚአብሔርን ትረዳለህ፤ አምላክንም ማወቅ ታገኛለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዚያን ጊዜ ጌታን መፍራትን ትገነዘባለህ፥ የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ሁሉ ብታደርግ እግዚአብሔርን መፍራት ምን እንደ ሆነ ታውቃለህ፤ የአምላክንም ዕውቀት ታገኛለህ። |
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ዕውቀት ለሚያደርጋት ሁሉ መልካም ናት። እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፥ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።
በድኅነታችን መዝገብ በሕግ ይሰበስቡአቸዋል፤ ጥበብና ምክር፥ ጽድቅም ከእግዚአብሔር ዘንድ ናቸው፤ እነዚህም የጽድቅ መዝገቦች ናቸው።
እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በፍጹምም ልባቸው ወደ እኔ ይመለሳሉና ሕዝቤ ይሆኑኛል፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።”
እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን፦ እግዚአብሔርን ዕወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል እግዚአብሔር። በደላቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኀጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና።”
ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን፥ ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኘኝ ይህ ነውና፥” ይላል እግዚአብሔር።
እንወቀው፤ እናውቀውም ዘንድ እግዚአብሔርን እንከተል፤ እንደ ወገግታም ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን፤ በምድርም ላይ እንደ መጀመሪያውና እንደ ኋለኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።
ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።
ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጠኝ፤ ወልድ ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም፤ አብም ማን እንደ ሆነ ከወልድ በቀር የሚያውቅ የለም። ወልድ ግን ለወደደው ይገልጥለታል።”
ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንህ አንተን፥ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘለዓለም ሕይወት ናት።
የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።