ምሳሌ 19:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቱን የሚያዋርድ እናቱንም የሚያሳድድ፥ አሳፋሪና ጐስቋላ ልጅ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቱን የሚዘርፍ፣ እናቱንም የሚያሳድድ፣ ዕፍረትና ውርደት የሚያመጣ ልጅ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቱን የሚያስከፋ እናቱንም የሚያሳድድ የሚያሳፍርና ጐስቋላ ልጅ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሳፋሪና አስነዋሪ የሆነ ልጅ አባቱን ያጒላላል፤ እናቱንም ከቤት ያባርራል። |
የተማረ ልጅ ብልህ ይሆናል። ሰነፍ ልጅ ግን ራሱን ተገዥ ያደርጋል። ብልህ ልጅ ከቃጠሎ ይድናል፤ ኀጢአተኛ ልጅ ግን በአውድማ ነፋስ የሚጨብጥ ይሆናል። ብልህ ልጅ በመከር ጊዜ ይሠራል። ሰነፍ ልጅ ግን በመከር ጊዜ ይተኛል።