የእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ ከእውነት ጋር ነው።
ከጽድቅ ጋራ ጥቂቱ ነገር፣ በግፍ ከሚገኝ ብዙ ትርፍ ይሻላል።
በጽድቅ የሚገኝ ጥቂት ነገር በዓመፅ ከሚገኝ ከብዙ ትርፍ ይሻላል።
ፍትሕን በማጓደል ከሚገኝ ብዙ ሀብት ይልቅ በእውነት የሚገኝ ጥቂት ነገር ይሻላል።
የጠላቶቼ መዘባበቻ አታድርገኝ ብያለሁና፥ እግሬም ቢሰናከል በእኔ ላይ ብዙ ነገርን ይናገራሉ።
እግዚአብሔርን በመፍራት የሚገኝ ጥቂት ሀብት እግዚአብሔርን ባለመፍራት ከሚገኝ ብዙ መዝገብ ይሻላል።
ጥል ካለበት የሰባ ፊሪዳ፥ ደስታና ፍቅር ያለበት የጎመን ወጥ ይሻላል።
ቅንነትን የሚሹ ሰላምን ያገኛሉ።
ኃጥእ ለክፉ ቀን ይጠበቃል።
ብዙ ደስታ ከሞላበትና ከክርክር ጋር የዐመፃ ፍሪዳ ካለበት ቤት ይልቅ፥ ከሰላም ጋር ደረቅ ቍራሽ ይሻላል።
በድካምና ነፋስን በመከተል ከሁለት እጅ ሙሉ ይልቅ አንድ እጅ ሙሉ በዕረፍት ይሻላል።
ቆቅ ጮኸች፤ ያልወለደችውንም ዐቀፈች፤ በዐመፅ ባለጠግነትን የሚሰበስብ ሰውም እንደዚሁ ነው፤ በእኩሌታ ዘመኑ ይተወዋል፤ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።
በውኑ በኃጢአተኛ ቤት የኃጢአት መዝገብ፥ የተጸየፈውም ውሸተኛ መስፈሪያ ገና አለ ይሆን?