ምሳሌ 16:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልካም ሽምግልና የክብር አክሊል ነው፥ እርሱም በጽድቅ መንገድ ይገኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሽበት የክብር ዘውድ ነው፤ የሚገኘውም በጽድቅ ሕይወት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሸበተ ጠጉር የክብር ዘውድ ነው፥ እርሱም በጽድቅ መንገድ ይገኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሽበት የክብር ዘውድ ነው። የሚገኘውም በተቀደሰ አኗኗር ነው። |
ከፍ ያለውን ተመልክተው ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፤ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፍሬም ሳይበተን፤ ሰው ወደ ዘለዓለም ቤቱ ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፤
“በሽበታሙ ፊት ተነሣ፤ ሽማግሌውንም አክብር፤ አምላክህን እግዚአብሔርንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።