ምሳሌ 16:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተሳዳቢዎች ጋር ምርኮን ከሚካፈል፥ በትሕትና ቍጣን የሚያርቅ ይሻላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተዋረደ መንፈስ ከተጨቈኑት ጋራ መሆን፣ ከትዕቢተኞች ጋራ ብዝበዛን ከመካፈል ይሻላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዕቡያን ጋር ምርኮ ከመካፈል ከትሑታን ጋር በተዋረደ መንፈስ መሆን ይሻላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከትዕቢተኞች ጋር የዘረፉትን አብሮ ከመካፈል ትሑት ሆኖ በድኽነት መኖር ይሻላል። |
ጠላትም፦ ‘አሳድጄ እይዛቸዋለሁ፤ ምርኮም እካፈላለሁ፤ ነፍሴንም አጠግባታለሁ፤ በሰይፌም እገድላለሁ፤ በእጄም እገዛለሁ’ አለ።
ቍጣዬን በኀጢአተኛ ሕዝብ ላይ እልካለሁ፤ ይማርኳቸውና ይበዘብዙአቸው ዘንድ፥ ከተሞችንም ይረግጡአቸውና እንደ ትቢያ ያደርጓቸው ዘንድ ሕዝቤን አዝዛለሁ።
ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፤ ከኀያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዐመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኀጢአት ተሸከመ፤ ስለ ኀጢአታቸውም ተሰጠ።
ለዘለዓለም በአርያም የሚኖር ስሙም ቅዱሰ ቅዱሳን የሆነ፥ በቅዱሳን አድሮ የሚኖር፥ ለተዋረዱት ትዕግሥትን የሚሰጥ፥ ልባቸውም ለተቀጠቀጠ ሕይወትን የሚሰጥ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
ምርኮውን ሲካፈል፥ በኀያላኑም ቸብቸቦ ላይ ወዳጆችን ሲወዳጅ ያገኙት አይደለምን? የሲሣራ ምርኮ በየኅብሩ ነበረ፤ የኅብሩም ቀለም የተለያየ ነበረ፤ የማረከውም ወርቀ ዘቦ ግምጃ በአንገቱ ላይ ነበረ።