እግዚአብሔርም መንግሥቱን በእጁ አጸና፤ ይሁዳም ሁሉ እጅ መንሻ ለኢዮሳፍጥ አመጣ፤ እጅግም ብዙ ብልጥግናና ክብር ሆነለት።
ምሳሌ 16:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉን የሚሠራም በንጉሥ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ የፍርድ ዙፋን በጽድቅ ይጸናልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፋትን ማድረግ ለነገሥታት አስጸያፊ ነው፤ ዙፋን የሚጸናው በጽድቅ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግፍን መሥራት በንጉሥ ዘንድ ጸያፍ ነገር ነው፥ ዙፋን በጽድቅ ይጸናልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንግሥት የሚጸናው በፍትሕ ስለ ሆነ ክፉ ሥራ በመሪዎች ዘንድ የተጠላ ነው። |
እግዚአብሔርም መንግሥቱን በእጁ አጸና፤ ይሁዳም ሁሉ እጅ መንሻ ለኢዮሳፍጥ አመጣ፤ እጅግም ብዙ ብልጥግናና ክብር ሆነለት።