ምሳሌ 13:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልካም ዕውቀት ሞገስንና ጥበብን ይሰጣል፤ የቸለልተኞች መንገድ ግን በጥፋት ውስጥ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካም ማስተዋል ሞገስን ታስገኛለች፤ የከዳተኞች መንገድ ግን አስቸጋሪ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካም እውቀት ሞገስን ይሰጣል፥ የወስላቶች መንገድ ግን ሸካራ ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አስተዋይ መሆን ያስከብራል፤ ከዳተኛነት ግን ወደ ጥፋት ያደርሳል። |
ክፋትሽ ይገሥጽሻል፤ ክዳትሽም ይዘልፍሻል፤ እኔን መተውሽም ክፉና መራራ ነገር መሆኑን ታውቂያለሽ፤ ትረጂማለሽ” ይላል አምላክሽ እግዚአብሔር፤ “መፈራቴም በአንቺ ዘንድ የለም፤ ይህም ደስ አላሰኘኝም” ይላል አምላክሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ከመከራውም ሁሉ አዳነው፤ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ሞገስንና ጥበብን ሰጠው፤ በግብፅና በቤቱ ሁሉ ላይ ቢትወደድ አድርጎ ሾመው።