La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 12:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የጻድቃን አሳብ ቅን ነው፤ ኃጥኣን ግን ሽንገላን ያስተምራሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የጻድቃን ሐሳብ ቀና ነው፤ የክፉዎች ምክር ግን ሸር አለበት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጻድቃን አሳብ ቅን ነው፥ የክፉዎች ምክር ግን ሽንገላ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእውነተኞች ሰዎች ሐሳብ የቀና ነው፤ የክፉዎች ምክር ግን አታላይነት ነው።

Ver Capítulo



ምሳሌ 12:5
20 Referencias Cruzadas  

የጻድቃን ምኞት መልካም ነው፤ የኃጥኣን ተስፋ ግን ይጠፋል።


ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤ ክፉ ሴት ግን ነቀዝ እንጨትን እንደሚበላ እንዲዚሁ ባሏን ትጐዳለች።


የኃጥኣን ምክር ተንኮል ነው። የቅኖች አፍ ግን ይታደጋቸዋል።


የዐዋቂዎች ጥበብ መንገዳቸውን ታውቃለች፤ የሰነፎች ስንፍና ግን ወደ ስሕተት ይመራል።


ሰነፍ በኀጢአት ይሞታል፤ ነፍሰ ገዳይ ሰውን ርኵሰቱ፥


ክፉ ሰው መን​ገ​ዱን፥ በደ​ለ​ኛም ዐሳ​ቡን ይተው፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ለስ፤ እር​ሱም ይም​ረ​ዋል፤ እርሱ ብዙ በደ​ላ​ች​ሁን ይተ​ው​ላ​ች​ኋ​ልና።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! ትድኚ ዘንድ ልብ​ሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። ክፉ አሳብ የሚ​ኖ​ር​ብሽ እስከ መቼ ነው?


“ምላ​ሳ​ቸ​ውን ለሐ​ሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በም​ድ​ርም በረቱ፤ ነገር ግን ለእ​ው​ነት አይ​ደ​ለም፤ ከክ​ፋት ወደ ክፋት ይሄ​ዳ​ሉና፥ እኔ​ንም አላ​ወ​ቁ​ምና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እያ​ን​ዳ​ንዱ በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ይሣ​ለ​ቃል በእ​ው​ነ​ትም አይ​ና​ገ​ርም፤ ሐሰት መና​ገ​ር​ንም ምላ​ሳ​ቸው ተም​ሮ​አል፤ በደሉ መመ​ለ​ስ​ንም እንቢ አሉ።


ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።


ኢየሱስንም በተንኰል ሊያስይዙት ሊገድሉትም ተማከሩ፤


ጊዜው ሳይ​ደ​ርስ ዛሬ ለምን ትመ​ረ​ም​ራ​ላ​ቸሁ? በጨ​ለማ ውስጥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም የሚ​ያ​በራ፥ የል​ብን አሳ​ብም የሚ​ገ​ልጥ ጌታ​ችን ይመ​ጣል፤ ያን​ጊዜ ሁሉም ዋጋ​ውን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይቀ​በ​ላል።


ነገር ግን በስ​ውር የሚ​ሠ​ራ​ውን አሳ​ፋሪ ሥራ እን​ተ​ወው፤ በተ​ን​ኰ​ልም አን​መ​ላ​ለስ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል በው​ሸት አን​ቀ​ላ​ቅል፤ ለሰ​ውም ሁሉ አር​አያ ስለ መሆን እው​ነ​ትን ገል​ጠን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ጽና።