ምሳሌ 10:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተማረ ልጅ ብልህ ይሆናል። ሰነፍ ልጅ ግን ራሱን ተገዥ ያደርጋል። ብልህ ልጅ ከቃጠሎ ይድናል፤ ኀጢአተኛ ልጅ ግን በአውድማ ነፋስ የሚጨብጥ ይሆናል። ብልህ ልጅ በመከር ጊዜ ይሠራል። ሰነፍ ልጅ ግን በመከር ጊዜ ይተኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰብሉን በበጋ የሚሰበስብ ጠቢብ ልጅ ነው፤ በመከር ጊዜ የሚተኛ ግን ውርደት ይከተለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በበጋ የሚያከማች ልጅ አስተዋይ ነው፥ በመከር የሚተኛ ግን እርሱ ራሱን ያስነውራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብልኅ ሰው መከሩን በወቅቱ ይሰበስባል፤ በመከር ወራት የሚተኛ ግን ውርደት ይደርስበታል። |
መብሉን በበጋ ይሰበስባል፥ በመከርም ጊዜ በሰፊ ቦታ ያስቀምጣል። ወይም ወደ ንብ ሂድ፥ ሠራተኛ እንደ ሆነች፥ መልካም ሥራንም እንደምትሠራ ዕወቅ፥ የደከመችበትንም ነገሥታትና ሌሎች ሰዎች ለጤንነት ይወስዱታል። በሁሉም ዘንድ የተወደደች ናት፥ የከበረችም ናት። በአካሏ ደካማ ናት፥ በሥራዋ ግን የጸናች ናት፥ ጥበብን አክብራ አሳየች።