ምሳሌ 10:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደስታ ከጻድቃን ጋር ትኖራለች፤ የኃጥኣን ተስፋ ግን ትጠፋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጻድቃን አለኝታ ደስታ ነው፤ የክፉዎች ተስፋ ግን ከንቱ ሆኖ ይቀራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቃን አለኝታ ደስታ ነው፥ የክፉዎች ተስፋ ግን ይጠፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደጋግ ሰዎች ተስፋ ወደ ደስታ ይመራቸዋል፤ የክፉዎች ተስፋ ግን ከንቱ ሆኖ ይቀራል። |
የተስፋ አምላክ እግዚአብሔርም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል በተስፋ ያበዛችሁ ዘንድ በእምነት ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይፈጽምላችሁ።
ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን በጸጋም የዘላለምን መጽናናት በጎንም ተስፋ የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን ልባችሁን ያጽናኑት፤ በበጎም ሥራና በቃል ሁሉ ያጽኑአችሁ።