ምሳሌ 10:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጻድቅ ምላስ የተፈተነ ብር ነው፤ የኃጥኣን ልብ ግን ይጐድላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጻድቅ አንደበት የነጠረ ብር ነው፤ የክፉ ሰው ልብ ግን ርባና የለውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቅ ምላስ የተፈተነ ብር ነው፥ የክፉ ልብ ግን ዋጋ ቢስ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደግ ሰው ንግግር እንደ ነጠረ ብር ነው፤ የክፉ ሰው አሳብ ግን ዋጋቢስ ነው። |
እግዚአብሔር አምላክም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ “ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰዎች ሥራ አልረግምም፤ በሰው ልብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖራል፤ ደግሞም ከዚህ ቀደም እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደገና አልመታም።
ሣርን እንደሚበላ ይበላል፥ ይጠጣልም፤ ወደ አንተም አታስገባው፥ ከእርሱ ጋርም እንጀራን አትብላ፥ ብላ፥ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ከአንተ ጋር አይደለም።