ምሳሌ 1:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚሰማኝ ግን በተስፋ ይኖራል፥ ከክፉም ሁሉ ያለ ድንጋጤ ያርፋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያዳምጠኝ ሁሉ ግን በሰላም ይኖራል፤ ክፉን ሳይፈራ ያለ ሥጋት ይቀመጣል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚሰማኝ ግን ተረጋግቶ ይቀመጣል፥ ከክፉም ሥጋት ያርፋል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔን የሚሰማ ግን ለሕይወቱ ዋስትና ይኖረዋል፤ ምንም የሚያስፈራው ነገር ሳይደርስበት በሰላም ይኖራል።” |
የበደለ ከጥንት ጀምሮ ከዚያም በፊት ኀጢአትን አድርጓል፥ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት በፊቱም ለሚፈሩት ደኅንነት እንዲሆን አውቃለሁና፤
ስሙኝ፤ ጎዳናዬን ተከተሉ፤ አድምጡኝም፤ ሰውነታችሁም በበረከት ትኖራለች፤ የታመነችዪቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።
ጦርነትንና ጠብን፥ ክርክርንም በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ አስቀድሞ ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ነውና፤ ነገር ግን ወዲያው የሚፈጸም አይደለም።”