La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ፊልጵስዩስ 2:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ስለ መሥ​ራት እስከ ሞት ደር​ሶ​አ​ልና፥ ከእኔ መል​እ​ክ​ትም እና​ንተ ያጐ​ደ​ላ​ች​ሁ​ትን ይፈ​ጽም ዘንድ ሰው​ነ​ቱን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱም እናንተ ልትሰጡኝ ያልቻላችሁትን አገልግሎት ለማሟላት ሲል ለሕይወቱ እንኳ ሳይሣሣ፣ ለክርስቶስ ሥራ ከሞት አፋፍ ደርሶ ነበርና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ምክንያቱም እናንተ ልትሰጡኝ ያልቻላችሁትን አገልግሎት ለመፈጸም ሕይወቱን አደጋ ላይ ጥሎ ለክርስተቶስ ሥራ ሲል ለሞት ተቃርቦ ነበርና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እናንተ በቅርብ ተገኝታችሁ ልታደርጉልኝ ያልቻላችሁትን ርዳታ እርሱ ለማሟላት ብሎ ስለ ክርስቶስ ሥራ ለሕይወቱ ሳይሳሳ ለሞት ተቃርቦ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በእኔ ዘንድ ካላችሁ አገልግሎት እናንተ ስለሌላችሁ የጎደለኝን እንዲፈጽም፥ በነፍሱ ተወራርዶ ከጌታ ሥራ የተነሣ እስከ ሞት ቀርቦአልና።

Ver Capítulo



ፊልጵስዩስ 2:30
15 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጸ​ጋ​ውን ወን​ጌል እን​ዳ​ስ​ተ​ምር ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የተ​ቀ​በ​ል​ሁ​ትን ሩጫ​ዬን እን​ድ​ጨ​ር​ስና መል​እ​ክ​ቴ​ንም እን​ድ​ፈ​ጽም ነው እንጂ ለሰ​ው​ነቴ ምንም አላ​ስ​ብ​ላ​ትም።


ስለ እኔ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ለመ​ከራ አሳ​ል​ፈው ሰጥ​ተ​ዋ​ልና፤ የማ​መ​ሰ​ግ​ና​ቸ​ውም እኔ ብቻ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ከአ​ሕ​ዛብ ያመኑ ምእ​መ​ናን ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​አ​ቸ​ዋል እንጂ።


ይህ የሚ​ፈ​ር​ሰው የማ​ይ​ፈ​ር​ሰ​ውን፥ ይህም የሚ​ሞ​ተው የማ​ይ​ሞ​ተ​ውን ይለ​ብስ ዘንድ አለ​ውና።


ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም በመጣ ጊዜ በእ​ና​ንተ ዘንድ ያለ ፍር​ሀት እን​ዲ​ኖር ተጠ​ን​ቀቁ፤ እንደ እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ይሠ​ራ​ልና።


እስ​ጢ​ፋ​ኖስ፥ ፈር​ዶ​ና​ጥ​ስና አካ​ይ​ቆስ በመ​ም​ጣ​ታ​ቸ​ውም ደስ ይለ​ኛል፤ እና​ንተ ያጐ​ደ​ላ​ች​ሁ​ትን እነ​ርሱ ፈጽ​መ​ዋ​ልና።


እኔ ግን እጥፍ ድርብ አወ​ጣ​ለሁ፤ ስለ ሕይ​ወ​ታ​ች​ሁም ሰው​ነ​ቴን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተ​ንም እጅግ ብወ​ዳ​ችሁ ራሴን ወደ​ድሁ።


ስለ​ዚ​ህም ሞት በእኛ ላይ፥ ሕይ​ወ​ትም በእ​ና​ንተ ላይ ይሠ​ራል።


ስለ ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ች​ሁም የአ​ም​ልኮ መሥ​ዋ​ዕ​ትን እሠ​ዋ​ለሁ። እነ​ሆም እኔ በእ​ና​ንተ ደስ ይለ​ኛል፤


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማረው፤ በኀ​ዘን ላይ ኀዘን እን​ዳ​ይ​ጨ​መ​ር​ብኝ ለእ​ኔም እንጂ ለእሱ ብቻ አይ​ደ​ለም።


በጌ​ታ​ችን እጅግ ደስ አለኝ፤ ቢሳ​ና​ችሁ እንኳ አሁ​ንም እን​ደ​ም​ታ​ስ​ቡ​ልኝ፥ ከዱሮ ጀምሮ ለእኔ ችግር ታስቡ፥ ትተ​ጉም ነበ​ርና።


ነገር ግን ሁሉ አለኝ፤ ይበ​ዛ​ል​ኝ​ማል፤ የመ​ዓዛ ሽታና የተ​ወ​ደደ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን ስጦ​ታ​ች​ሁን ከአ​ፍ​ሮ​ዲጡ ተቀ​ብዬ አሟ​ል​ቻ​ለሁ።


እኔስ በወንጌል እስራት ስለ አንተ እንዲያገለግለኝ ለራሴ ላስቀረው እፈቅድ ነበር፤


እነርሱም በበጉ ደም በምስክራቸውም ቃል ድል ነሡት፤ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም።