ሌዋውያንም ከሠላሳ ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ ተቈጠሩ፤ ቍጥራቸውም በእያንዳንዱ ነፍስ ወከፍ ሲቈጠሩ ሠላሳ ስምንት ሺህ ነበረ።
ዘኍል 8:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሌዋውያን ሕግ ይህ ነው፤ ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በምስክሩ ድንኳን ሥራ ያገለግሉ ዘንድ ይገባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሌዋውያንን የሚመለከተው ደንብ ይህ ነው፤ በመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ለመሳተፍ ሃያ ዐምስት ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ወንዶች ይመጣሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በሌዋውያን ላይ ይህ ተፈጻሚ ይሆንባቸዋል፤ ዕድሚያቸው ሀያ አምስት ዓመት የሆናቸውና ከዚያም በላይ ያሉት የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ለመፈጸም ይገባሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ኻያ አምስት ዓመት የሞላውና ከዚያም በላይ የሆነ ሌዋዊ ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አገልግሎቱን ይፈጽማል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሌዋውያን ሕግ ይህ ነው፤ ከሀያ አምስት ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት በመገናኛው ድንኳን ሥራ ያገለግሉ ዘንድ ይገባሉ። |
ሌዋውያንም ከሠላሳ ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ ተቈጠሩ፤ ቍጥራቸውም በእያንዳንዱ ነፍስ ወከፍ ሲቈጠሩ ሠላሳ ስምንት ሺህ ነበረ።
በየአባቶቻቸውም ቤት ለተቈጠሩ ካህናት፥ ከሃያ ዓመትም ወደ ላይ ላሉ በየሥርዐታቸውና በየሰሞናቸው ለተቈጠሩ ሌዋውያን፥
ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ላይ ዕዳ እንዳይሆንባቸው ሌዋውያን በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ ፊት ለፊት ይስፈሩ፤ ሌዋውያን የምስክሩን ድንኳን ሕግ ይጠብቁ።”
የምስክሩን ድንኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠራቸው።
ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በምስክሩ ድንኳን ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡበትን ሁሉ ትለያለህ።
የምስክሩን ድንኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠራቸው።
በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ወደ አገልግሎት የገቡት ሁሉ ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቈጠሯቸው።
የሚያገለግልም ምግቡን ያገኝ ዘንድ ነው፤ ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? መንጋውንስ ጠብቆ ወተቱን የማይጠጣ ማን ነው?