ለአምላኩ ያደረገው ብፅዐት በራሱ ላይ ነውና አባቱ፥ ወይም እናቱ፥ ወይም ወንድሙ፥ ወይም እኅቱ ሲሞቱ ሰውነቱን አያርክስባቸው።
ዘኍል 6:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በብፅዐቱ ወራት ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራሱን በለየበት ጊዜ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራሱን በለየበት ወራት ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናዝራዊ እስከ ሆነ ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ (የተቀደሰ) ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራሱን የተለየ ባደረገበት ወራት ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው። |
ለአምላኩ ያደረገው ብፅዐት በራሱ ላይ ነውና አባቱ፥ ወይም እናቱ፥ ወይም ወንድሙ፥ ወይም እኅቱ ሲሞቱ ሰውነቱን አያርክስባቸው።
“ሰውም በአጠገቡ ድንገት ቢሞት የራሱ ብፅዐት ይረክሳል፤ እርሱ በሚነጻበት ቀን ራሱን ይላጭ፤ በሰባተኛው ቀን ይላጨው።