እንዳይረክሱም ወደ ሞተ ሰው አይግቡ፤ ነገር ግን ለአባት፥ ወይም ለእናት፥ ወይም ለወንድ ልጅ፥ ወይም ለሴት ልጅ፥ ወይም ለወንድም፥ ወይም ላልተዳረች እኅት ይርከሱ።
ዘኍል 6:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአምላኩ ያደረገው ብፅዐት በራሱ ላይ ነውና አባቱ፥ ወይም እናቱ፥ ወይም ወንድሙ፥ ወይም እኅቱ ሲሞቱ ሰውነቱን አያርክስባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራሱን ለእግዚአብሔር የለየበት ምልክት በራሱ ላይ ስላለ አባቱም ይሁን እናቱ፣ ወንድሙም ይሁን እኅቱ ቢሞቱ ለእነርሱ ሲል እንኳ ራሱን አያርክስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአምላኩ ያደረገው ቅድስና በራሱ ላይ ነውና አባቱ ወይም እናቱ ወይም ወንድሙ ወይም እኅቱ ሲሞቱ ራሱን ስለ እነርሱ አያርክስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአምላኩ ያቀረበው የናዝራዊነት ስእለት በራሱ ላይ ስለ ሆነ አባቱ ወይም እናቱ፥ ወንድሙ ወይም እኅቱ ቢሞቱ አስከሬናቸውን በመንካት ራሱን አያርክስ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአምላኩ ያደረገው ስእለት በራሱ ላይ ነውና አባቱ ወይም እናቱ ወይም ወንድሙ ወይም እኅቱ ሲሞቱ ሰውነቱን አያርክስባቸው። |
እንዳይረክሱም ወደ ሞተ ሰው አይግቡ፤ ነገር ግን ለአባት፥ ወይም ለእናት፥ ወይም ለወንድ ልጅ፥ ወይም ለሴት ልጅ፥ ወይም ለወንድም፥ ወይም ላልተዳረች እኅት ይርከሱ።