በስእለቱ ወራትም ሁሉ ለእግዚአብሔር ይቀደሳል፤ የአንድ ዓመትም ተባት ጠቦት ለበደል መሥዋዕት ያምጣ፤ ስእለቱ ግን ረክሶአልና ያለፈው ወራት ሁሉ አይቈጠርለትም።
ዘኍል 6:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የተሳለው ሰው ሕግ ይህ ነው፤ የስእለቱ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ራሱ ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ይቅረብ፤ ቍርባኑንም ለእግዚአብሔር ያቅርብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘እንግዲህ ናዝራዊ የመለየቱ ጊዜ ሲያበቃ ሥርዐቱ ይህ ነው፤ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ እንዲመጣ ይደረጋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የመለየቱ ወራት በተፈጸመ ጊዜ የናዝራዊው ሕግ ይህ ነው፤ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይቅረብ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ናዝራዊ የናዝራዊነት ስእለቱን ሲጨርስ የሚፈጽመው ሕግ ይህ ነው፦ ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ በር ሄዶ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመለየቱ ወራት በተፈጸመ ጊዜ የናዝራዊው ሕግ ይህ ነው፤ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይቅረብ፤ |
በስእለቱ ወራትም ሁሉ ለእግዚአብሔር ይቀደሳል፤ የአንድ ዓመትም ተባት ጠቦት ለበደል መሥዋዕት ያምጣ፤ ስእለቱ ግን ረክሶአልና ያለፈው ወራት ሁሉ አይቈጠርለትም።
ያንጊዜም ጳውሎስ ሰዎችን ይዞ በማግሥቱ ከእነርሱ ጋር ነጻ። የመንጻታቸውንም ወራት መድረሱን ከነገራቸው በኋላ ሁሉም እየአንዳንዳቸው መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ ይዞአቸው ገባ።