La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 4:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ወደ አገ​ል​ግ​ሎት የገ​ቡ​ትን ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉ​ትን ቈጠ​ሩ​አ​ቸው፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከሠላሳ እስከ ዐምሳ ዓመት ሆኗቸው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለማገልገል የመጡት ወንዶች ሁሉ፣

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራን ለመሥራት ወደ አገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቈጠሩአቸው፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ወደ አገልግሎት የገቡትን ሁሉ ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ያሉትን ቈጠሩአቸው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ወደ አገልግሎት የገቡትን ሁሉ ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቈጠሩአቸው፤

Ver Capítulo



ዘኍል 4:35
15 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት አገ​ል​ግ​ሎት በሠሩ ከሃያ አም​ስት ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ በነ​በሩ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በስ​ማ​ቸው በተ​ቈ​ጠ​ሩት ላይ የአ​ባ​ቶች ቤት አለ​ቆች የሆ​ኑት በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነ​ዚህ ነበሩ።


ሌዋ​ው​ያ​ንም ከሠ​ላሳ ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ ተቈ​ጠሩ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ነፍስ ወከፍ ሲቈ​ጠሩ ሠላሳ ስም​ንት ሺህ ነበረ።


የካ​ህ​ና​ቱ​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ክፍ​ላ​ቸ​ውን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በት ሥራ ሁሉ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በት ዕቃ ሁሉ፥ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ ለሚ​ሆ​ነ​ውም፥


የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​ትን ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠ​ራ​ቸው።


ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​በ​ትን ሁሉ ትለ​ያ​ለህ።


የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​ትን ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠ​ራ​ቸው።


ሙሴና አሮ​ንም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አለ​ቆች የቀ​ዓ​ትን ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች ቈጠ​ሩ​አ​ቸው።


በየ​ወ​ገ​ና​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሁለት ሺህ ሰባት መቶ አምሳ ነበሩ።


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የገ​ቡት ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉ​ትን ቈጠ​ሩ​አ​ቸው።


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ወደ አገ​ል​ግ​ሎት የገ​ቡት ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉ​ትን ቈጠ​ሯ​ቸው።


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ሥራ​ውን ለመ​ሥ​ራ​ትና ዕቃ​ውን ለመ​ሸ​ከም የገ​ቡት ሁሉ፥ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉት፥


የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዕድ​ሜዉ ሠላሳ ዓመት ያህል ነበር፤ የዮ​ሴፍ ልጅም ይመ​ስ​ላ​ቸው ነበር።


በትዕቢት ተነፍቶ በዲያቢሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ፥ አዲስ ክርስቲያን አይሁን።