“ምድሪቱን ለእስራኤል ልጆች ርስት አድርጎ በዕጣ ከፍሎ ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር ጌታችንን አዘዘው፤ እግዚአብሔርም የወንድማችንን የሰለጰዓድን ርስት ለሴቶች ልጆቹ ይሰጣቸው ዘንድ ጌታችንን አዘዘው።
ዘኍል 36:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሌላም ከእስራኤል ልጆች ነገድ ባል ቢያገቡ፥ ርስታቸው ከአባቶቻችን ርስት ይነቀላል፤ እነርሱም ለሚገቡበት ለሌላው ነገድ ርስት ይጨመራል፤ እንደዚህም የርስታችን ዕጣ ይጐድላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሌሎች የእስራኤል ነገዶች ባል ቢያገቡ ድርሻቸው ከእኛ የዘር ርስት ላይ ተወስዶ የሚያገቧቸው ሰዎች ላሉበት ነገድ ይተላለፋል፤ ይህ ከሆነ ደግሞ በዕጣ ከተደለደለልን ርስት ላይ ከፊሉ ሊቀነስብን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሌላም ከእስራኤል ልጆች ነገድ ባል ቢያገቡ፥ ርስታቸው ከአባቶቻችን ርስት ይወሰዳል፥ እነርሱም ወደ አሉበት ወደ ለሌላው ነገድ ርስት ይጨመራል፤ እንደዚህም ከርስታችን ዕጣ ይወሰዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እነርሱ ከሌላ ነገድ የሆኑ ወንዶችን ቢያገቡ ርስታቸው የዚያ ነገድ መሆን እንደሚገባውና የእኛም ድርሻ ሊቀነስ እንደሚችል አስታውስ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሌላም ከእስራኤል ልጆች ነገድ ባል ቢያገቡ፥ ርስታቸው ከአባቶቻችን ርስት ይነቀላል፥ እነርሱም ለሚሆኑበት ለሌላው ነገድ ርስት ይጨመራል፤ እንደዚህም የርስታችን ዕጣ ይጐድላል። |
“ምድሪቱን ለእስራኤል ልጆች ርስት አድርጎ በዕጣ ከፍሎ ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር ጌታችንን አዘዘው፤ እግዚአብሔርም የወንድማችንን የሰለጰዓድን ርስት ለሴቶች ልጆቹ ይሰጣቸው ዘንድ ጌታችንን አዘዘው።
ለእስራኤልም ልጆች ኢዮቤልዩ በሆነ ጊዜ ርስታቸው ሴቶቹ ወደ አገቡበት ወደ ሌላ ነገድ ርስት ይጨመራል፤ እነሆ፥ ርስታቸው ከአባቶቻችን ነገድ ርስት ይጐድላል።”