La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 35:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወይም በጥ​ላቻ እስ​ኪ​ሞት ድረስ በእጁ ቢመ​ታው፥ የመ​ታው ፈጽሞ ይገ​ደል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ባለ ደሙ ወይም ተበ​ቃዩ ባገ​ኘው ጊዜ ነፍሰ ገዳ​ዩን ይግ​ደ​ለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወይም ደግሞ በጥላቻ ተነሣሥቶ በእጁ ቢመታውና ቢሞት፣ ያ ሰው በሞት ይቀጣል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ደም መላሹም ገዳዩን ባገኘው ጊዜ ይግደለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወይም በጥላቻ እስኪሞት ድረስ በእጁ ቢመታው፥ የመታው ፈጽሞ ይገደል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ደም ተበቃዩ ባገኘው ጊዜ ነፍሰ ገዳዩን ይግደለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወይም በጠላትነት ተነሣሥቶ በቡጢ በመምታት ቢገድለው የግድያ ወንጀል ስለ ፈጸመ መገደል አለበት፤ የሟች ቅርብ ዘመድ ነፍሰ ገዳዩን የመግደል መብት ይኖረዋል፤ ስለዚህ ባገኘው ጊዜ ሊገድለው ይችላል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወይም በጥላቻ እስኪሞት ድረስ በእጁ ቢመታው፥ የመታው ፈጽሞ ይገደል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ደም ተበቃዩ ባገኘው ጊዜ ነፍሰ ገዳዩን ይግደለው።

Ver Capítulo



ዘኍል 35:21
7 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ ዛሬ ከም​ድር ፊት ከአ​ሳ​ደ​ድ​ኸኝ፥ ከፊ​ትህ እሰ​ወ​ራ​ለሁ፤ በም​ድ​ርም ላይ ኮብ​ላ​ይና ተቅ​በ​ዝ​ባዥ እሆ​ና​ለሁ፤ የሚ​ያ​ገ​ኘ​ኝም ሁሉ ይገ​ድ​ለ​ኛል።”


ነፍ​ሳ​ችሁ ያለ​ች​በ​ትን ደማ​ች​ሁን ከአ​ራ​ዊት ሁሉ እጅ እሻ​ዋ​ለሁ፤ ከሰ​ውም እጅ፥ ከሰው ወን​ድም እጅ፥ የሰ​ውን ነፍስ እሻ​ለሁ።


ያችም ሴት፥ “ለመ​ግ​ደል ባለ ደሞች እን​ዳ​ይ​በዙ፤ ልጄ​ንም እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉ​ብኝ ንጉሥ ፈጣ​ሪው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያስብ” አለች። እር​ሱም፥ “የል​ጅ​ሽስ አን​ዲት የራሱ ጠጕር በም​ድር ላይ እን​ዳ​ት​ወ​ድቅ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን” አላት።


በአ​መ​ን​ዝ​ሮ​ችና በደም አፍ​ሳ​ሾች በቀል እበ​ቀ​ል​ሻ​ለሁ፤ በመ​ዓ​ትና በቅ​ን​አት ደምም አስ​ቀ​ም​ጥ​ሻ​ለሁ።


ደም ተበ​ቃዩ ራሱ ነፍሰ ገዳ​ዩን ይግ​ደል፤ ባገ​ኘው ጊዜ ይግ​ደ​ለው።


ጥል ቢጣ​ላው፥ ወይም ሸምቆ አን​ዳች ነገር ቢጥ​ል​በት፥ ቢሞ​ትም፥


“ነገር ግን ያለ ጥላቻ ድን​ገት ቢደ​ፋው፥ ሳይ​ሸ​ም​ቅም አን​ዳች ነገር ቢጥ​ል​በት፥