Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 35:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ወይም በጠላትነት ተነሣሥቶ በቡጢ በመምታት ቢገድለው የግድያ ወንጀል ስለ ፈጸመ መገደል አለበት፤ የሟች ቅርብ ዘመድ ነፍሰ ገዳዩን የመግደል መብት ይኖረዋል፤ ስለዚህ ባገኘው ጊዜ ሊገድለው ይችላል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ወይም ደግሞ በጥላቻ ተነሣሥቶ በእጁ ቢመታውና ቢሞት፣ ያ ሰው በሞት ይቀጣል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ደም መላሹም ገዳዩን ባገኘው ጊዜ ይግደለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ወይም በጥላቻ እስኪሞት ድረስ በእጁ ቢመታው፥ የመታው ፈጽሞ ይገደል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ደም ተበቃዩ ባገኘው ጊዜ ነፍሰ ገዳዩን ይግደለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ወይም በጥ​ላቻ እስ​ኪ​ሞት ድረስ በእጁ ቢመ​ታው፥ የመ​ታው ፈጽሞ ይገ​ደል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ባለ ደሙ ወይም ተበ​ቃዩ ባገ​ኘው ጊዜ ነፍሰ ገዳ​ዩን ይግ​ደ​ለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ወይም በጥላቻ እስኪሞት ድረስ በእጁ ቢመታው፥ የመታው ፈጽሞ ይገደል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ደም ተበቃዩ ባገኘው ጊዜ ነፍሰ ገዳዩን ይግደለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 35:21
7 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ ዛሬ ከምድር አባረርከኝ፤ ከፊትህም እሰወራለሁ፤ በምድርም ላይ ስደተኛና ተንከራታች እሆናለሁ፤ እንግዲህ ማንም ሰው ቢያገኘኝ ይገድለኛል።”


ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ በተጠያቂነት ላይ እሻዋለሁ፤ ከእንስሶች ሁሉና ከሰውም ላይ እሻዋለሁ፤ ከሰው ሁሉ የሰውን ሕይወት እሻዋለሁ።


እርስዋም “ንጉሥ ሆይ! የልጄን ሞት ለመበቀል ኀላፊነት የተቀበለው ዘመዴ ሌላውን ልጄን በመግደል የባሰ ወንጀል እንዳይፈጽም ታደርገው ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ” አለችው። ንጉሥ ዳዊትም “በልጅሽ ላይ ጒዳት መድረስ ይቅርና ከራስ ጠጒሩ እንኳ አንዲቱ መሬት ላይ እንደማትወድቅ በሕያው እግዚአብሔር ስም ቃል እገባልሻለሁ” አላት።


እኔ በአንቺ ላይ፥ ዝሙት በፈጸሙና ሕይወት ባጠፉ ሴቶች ላይ የሚፈረደውን ፍርድ እፈርድብሻለሁ፤ አንቺን በቅናቴና በቊጣዬ አጠፋሻለሁ።


የሟቹ ቅርብ ዘመድ ነፍሰ ገዳዩን የመግደል መብት ይኖረዋል፤ ስለዚህ ባገኘው ጊዜ ሊገድለው ይችላል።


“አንድ ሰው ሌላውን ሰው በጥላቻ ቢገፋው ወይም ሸምቆ አንዳች ነገር ቢወረውርበትና ይህ አድራጎቱ ሞትን ቢያስከትል፥


“ነገር ግን አንድ ሰው ገፍትሮ በመጣልም ሆነ አንዳች ነገር በላዩ በመወርወር ሌላ ሰው የሚገድለው ከጥላቻ የተነሣ ሳይሆን በድንገት ተሳስቶ ከሆነ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos