እነሆም፥ ዘመዶች ሁሉ በባሪያህ ላይ ተነሡ፤ ስለ ገደለው ስለ ወንድሙ ነፍስ እንገድለው ዘንድ ወንድሙን የገደለውን አውጪ አሉኝ፤ እንዲሁም ደግሞ ለባሌ ስምና ዘር በምድር ላይ እንዳይቀር ወራሹን የቀረውን መብራቴን ያጠፋሉ፤”
ዘኍል 35:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሰ ገዳዩ በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስከሚቆም ድረስ እንዳይሞት፥ ከተሞቹ ከደም ተበቃይ የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህም፣ ነፍሰ ገዳዩ በማኅበሩ ዘንድ ለፍርድ ከመቅረቡ በፊት እንዳይሞት ከደም ተበቃዩ የሚሸሽባቸው የመማፀኛ ከተሞች ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሰ ገዳዩ በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ እንዳይሞት፥ ከተሞቹ ከደም ተበቃይ የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ከሚፈልግ ከሟቹ ዘመድ ሊሰወር ይችላል፤ በግድያ ወንጀል የተከሰሰ ሰው ለፍርድ ሳይቀርብ መገደል የለበትም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍሰ ገዳዩ በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ እንዳይሞት፥ ከተሞቹም ከደም ተበቃይ የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ። |
እነሆም፥ ዘመዶች ሁሉ በባሪያህ ላይ ተነሡ፤ ስለ ገደለው ስለ ወንድሙ ነፍስ እንገድለው ዘንድ ወንድሙን የገደለውን አውጪ አሉኝ፤ እንዲሁም ደግሞ ለባሌ ስምና ዘር በምድር ላይ እንዳይቀር ወራሹን የቀረውን መብራቴን ያጠፋሉ፤”
ባለ ደሙ ነፍሰ ገዳዩን በልቡ ተናድዶ እንዳያሳድደው መንገዱም ሩቅ ስለሆነ አግኝቶ እንዳይገድለው፥ አስቀድሞ ጠላቱ አልነበረምና ሞት አይገባውም።
በማኅበሩ ፊት እስኪቆምና እስኪመረመር ድረስ ባለደሙ እንዳይገድለው ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲማፀን፥ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ፥ በመካካላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ የተመረጡ ከተሞች እነዚህ ናቸው።