ዘኍል 34:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሮቤልም ልጆች ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት፥ የጋድም ልጆች ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ርስታቸውን ወርሰዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሮቤል ነገድ ቤተ ሰቦች፣ የጋድ ነገድ ቤተ ሰቦች እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስታቸውን ተቀብለዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሮቤልም ልጆች ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት፥ የጋድም ልጆች ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ርስታቸውን ወርሰዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሮቤልና የጋድ ነገዶች፥ እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ በየቤተሰባቸው በመከፋፈል፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሮቤልም ልጆች ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት፥ የጋድም ልጆች ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ርስታቸውን ወርሰዋል። |
ሙሴም ለጋድ ልጆችና ለሮቤል ልጆች፥ ለዮሴፍም ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ፥ የአሞሬዎናውያንን ንጉሥ የሴዎንን መንግሥት፥ የባሳንንም ንጉሥ የዐግን መንግሥት፥ ምድሪቱንም፥ ከተራሮችም ጋር ከተሞችን፥ በዙሪያቸውም ያሉትን የምድሪቱን ከተሞች ሰጣቸው።
በዚያ ከሕዝቡ ገዦች ጋር የተሰበሰቡ የአለቆች ምድር እንደ ተከፈለች፥ የመጀመሪያውን ፍሬ አየ፤ እግዚአብሔርም ጽድቁን፥ ፍርዱንም ከእስራኤል ጋር አደረገ።
ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከግብፅ ከአንተ የጸኑትን ታላላቆቹን አሕዛብ በፊትህ እንዲያወጣ፥ አንተንም እንዲያገባህ፥ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ እንዲሰጥህ፥