ዘኍል 32:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን እግዚአብሔር ተቈጣ፤ እንዲህም ብሎ ማለ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ቍጣ ነደደ፤ እንዲህም ሲል ማለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን የጌታ ቁጣ ነደደ እንዲህም ብሎ ማለ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን እግዚአብሔር እጅግ ተቈጥቶ እንዲህ አለ፤ ‘በእኔ በመተማመን ስላልጸኑ፥ ከግብጽ ምድር ከወጡት ዕድሜአቸው ኻያ ዓመት የሞላቸውና ከዚያም በላይ የሆኑ ሁሉ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር ከቶ እንደማይገቡ ምዬአለሁ።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ቁጣ ነደደ፥ |
ወተትና ማርም ወደምታፈስሰው ከምድር ሁሉ ወደምታምር ወደ ሰጠኋቸው ምድር እንዳላገባቸው በምድረ በዳ በእነርሱ ላይ ፈጽሜ እጄን አነሣሁ።
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “እኒህ ሕዝብ እስከ መቼ ያስቈጡኛል? በፊታቸውስ ባደረግሁት ተአምራት ሁሉ እስከ መቼ አያምኑብኝም?
በእውነት ለአባቶቻቸው የማልሁላቸውን ምድር አያዩም፤ ከእኔ ጋር በዚህ ላሉ መልካምንና ክፉን ለይተው ለማያውቁ ልጆቻቸው፥ የሚያውቀው ለሌለ ለታናሹ ሁሉ ያችን ሀገር እሰጣታለሁ፤ ለጥፋት ያነሳሱኝ ሁሉ አያዩአትም።
በድኖቻችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃሉ፤ የተቈጠራችሁ ሁሉ፥ እንደ ቍጥራችሁ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ የሆነ ሁሉ፥ እናንተ ያጕረመረማችሁብኝ፥