በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው፥ ከሌዋውያን ወንዶች ሁሉ ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ በየወገናቸው የተቈጠሩት ሁሉ ሃያ ሁለት ሺህ ነበሩ።
ዘኍል 3:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም የተቈጠሩ ወንዶች በኵሮች ሁሉ በየስማቸው ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ ሃያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሆኗቸው በየስማቸው የተመዘገቡት ወንድ በኵሮች ሁሉ ብዛታቸው ሃያ ሁለት ሺሕ ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም የተቈጠሩ የወንድ በኩር ሁሉ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ዕድሜው አንድ ወር የሞላውና ከዚያም በላይ ያለው የተቈጠሩት ሀያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕድሜአቸው አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸውን በኲር ሆነው የተወለዱትን ወንዶች ሁሉ በስማቸው ዝርዝር መሠረት ኻያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም የተቈጠሩ ወንዶች በኵሮች ሁሉ የበስማቸው ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ ሀያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ነበሩ። |
በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው፥ ከሌዋውያን ወንዶች ሁሉ ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ በየወገናቸው የተቈጠሩት ሁሉ ሃያ ሁለት ሺህ ነበሩ።