ዘኍል 3:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም ወንዶች ሁሉ እንደ ቍጥራቸው ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ የተቈጠሩት ስድስት ሽህ አምሳ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሆኗቸው የተቈጠሩት ወንዶች ሁሉ ብዛታቸው ስድስት ሺሕ ሁለት መቶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም ወንዶች ሁሉ እንደ ቁጥራቸው ዕድሜው አንድ ወር የሞላውና ከዚያም በላይ ያለው የተቈጠሩት ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱም ዕድሜው አንድ ወር ከሆነው ሕፃን አንሥቶ፥ የተቈጠሩት የወንዶች ብዛት ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም ወንዶች ሁሉ እንደ ቍጥራቸው ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ የተቈጠሩት ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። |
ከይሁዳ ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። እነዚህም አስቀድመው ይጓዛሉ።