ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ላይ ዕዳ እንዳይሆንባቸው ሌዋውያን በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ ፊት ለፊት ይስፈሩ፤ ሌዋውያን የምስክሩን ድንኳን ሕግ ይጠብቁ።”
ዘኍል 3:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጌድሶን ልጆች ከድንኳን በኋላ በባሕር በኩል ይሰፍራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጌርሶን ጐሣዎች በምዕራብ በኩል ከማደሪያው ድንኳን ጀርባ ይሰፍራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌድሶናውያን ወገኖች ከማደሪያው በስተጀርባ በምዕራብ በኩል ይሰፍራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጌርሾናውያን ወገን የሚሰፍረው ከድንኳኑ በስተጀርባ በምዕራብ በኩል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጌድሶናውያን ወገኖች ከማደሪያው በኋላ በምዕራብ በኩል ይሰፍራሉ። |
ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ላይ ዕዳ እንዳይሆንባቸው ሌዋውያን በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ ፊት ለፊት ይስፈሩ፤ ሌዋውያን የምስክሩን ድንኳን ሕግ ይጠብቁ።”
“ከዚያም በኋላ የምስክሩ ድንኳን፥ በሰፈሮቹም መካከል የሌዋውያን ወገን ይጓዛል፤ እንደ አሰፋፈራቸው ሰው ሁሉ በየስፍራው፥ በየዓላማውም ይጓዛሉ።