የእህል ቍርባናቸውንም በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለአንድ ወይፈን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአውራውም በግ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ፥
ዘኍል 28:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰባቱም ጠቦቶች ለእያንዳንዱ ጠቦት ከመስፈሪያው ዐሥረኛ እጅ ታቀርባላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰባቱም የበግ ጠቦቶች ከእያንዳንዳቸው ጋራ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት አዘጋጁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሰባቱም ጠቦቶች ለእያንዳንዱ ጠቦት ከመስፈሪያው አሥረኛ እጅ ታቀርባላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእያንዳንዱም ጠቦት ጋር አንድ ኪሎ ዱቄት ታቀርባላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሰባቱም ጠቦቶች ለእያንዳንዱ ጠቦት ከመስፈሪያው አሥረኛ እጅ ታቀርባላችሁ። |
የእህል ቍርባናቸውንም በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለአንድ ወይፈን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአውራውም በግ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ፥