“በስምንተኛው ቀን ነውር የሌለባቸውን፥ ዓመት የሞላቸውን ሁለት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ ነውር የሌለባትንም አንዲት የዓመት እንስት የበግ ጠቦት፥ ስለ እህልም ቍርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ፥ በዘይት የተለወሰ መልካም የስንዴ ዱቄት፥ አንድ ማሰሮ ዘይትም ይወስዳል።
ዘኍል 28:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእህል ቍርባናቸውንም በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለአንድ ወይፈን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአውራውም በግ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእያንዳንዱም ወይፈን ጋራ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ ሦስት ዐሥረኛ ልም ዱቄት፣ ከአውራውም በግ ጋራ የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ ልም ዱቄት አቅርቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእህል ቁርባናቸውንም በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለአንድ ወይፈን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአውራውም በግ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተገቢ የሆነውንም የእህል ቊርባን በወይራ ዘይት የተለወሰ ምርጥ ዱቄት አቅርቡ፤ ይኸውም ከእያንዳንዱ ኰርማ ጋር ሦስት ኪሎ ዱቄት፥ ከአውራው በግ ጋር ሁለት ኪሎ ዱቄት፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእህል ቍርባናቸውንም በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለአንድ ወይፈን ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአውራውም በግ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ፥ |
“በስምንተኛው ቀን ነውር የሌለባቸውን፥ ዓመት የሞላቸውን ሁለት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ ነውር የሌለባትንም አንዲት የዓመት እንስት የበግ ጠቦት፥ ስለ እህልም ቍርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ፥ በዘይት የተለወሰ መልካም የስንዴ ዱቄት፥ አንድ ማሰሮ ዘይትም ይወስዳል።
በእሳትም የተደረገውን ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ከላሞች ሁለት በሬዎች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነውር የሌለባቸው ይሁኑላችሁ።