ሞዓብም የምድያምን ሽማግሌዎች፥ “በሬ የለመለመውን ሣር እንደሚጨርስ ይህ ሠራዊት በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ይጨርሳል” አላቸው። በዚያን ጊዜ የሶፎር ልጅ ባላቅ የሞዓብ ንጉሥ ነበረ።
ዘኍል 25:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድያማውያንን አስጨንቋቸው፤ ግደሉአቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ምድያማውያንን እንደ ጠላት ቈጥራችሁ ፍጇቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ምድያማውያን እንደ ጠላት ቁጠሩአቸው እነርሱንም ድል ንሱአቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በምድያማውያን ላይ አደጋ ጥላችሁ ደምስሱአቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፌጎር በመቅሠፍቱ ቀን ስለተገደለችው ስለ ምድያም አለቃ ልጅ ስለ እኅታቸው ስለ ከስቢ በፌጎር ምክንያት በሸነገሉአችሁ ሽንገላ አስጨንቀዋችኋልና ምድያማውያንን አስጨንቁአቸው ግደሉአቸውም። |
ሞዓብም የምድያምን ሽማግሌዎች፥ “በሬ የለመለመውን ሣር እንደሚጨርስ ይህ ሠራዊት በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ይጨርሳል” አላቸው። በዚያን ጊዜ የሶፎር ልጅ ባላቅ የሞዓብ ንጉሥ ነበረ።
ስለ ምድያም አለቃ ልጅ ስለ እኅታቸው ስለ ከስቢ በፌጎር ምክንያት በሸነገሉአችሁ ሽንገላ አስጨንቀዋችኋልና።”
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግዚአብሔርም በምድያም እጅ ሰባት ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው።