ሎጥም ዓይኖቹን አነሣ፤ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።
ዘኍል 24:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደሚጋርዱ ዛፎች፥ በወንዝ ዳር እንዳሉ የተክል ቦታዎች፥ እግዚአብሔር እንደ ተከላቸው ድንኳኖች በውኃም ዳር እንዳሉ ዝግባዎች ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንደ ሸለቆዎች፣ በወንዝ ዳር እንዳሉም የአትክልት ስፍራዎች ተዘርግተዋል፤ በእግዚአብሔር እንደ ተተከሉ አደሶች፣ በውሃም አጠገብ እንዳሉ ዝግባዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደፊትም ተዘርግቶ እንዳለው ሸለቆች፥ በወንዝ ዳር እንዳሉ አትክልቶች፥ ጌታ እንደ ተከለው ዓልሙን በውኃም ዳር እንዳሉ ዝግባዎች ተዘርግተዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እንደ ተዘረጉ ሸለቆዎችና፥ በወንዝ ዳር እንደሚገኙ የአትክልት ቦታዎች፥ እግዚአብሔር እንደ ተከለው የሬት ዛፍ ወይም በውሃ ዳር እንደ በቀለ የሊባኖስ ዛፍ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ሸለቆች፥ በወንዝ ዳር እንዳሉ አትክልቶች፥ እግዚአብሔር እንደ ተከለው እሬት በውኃም ዳር እንዳሉ ዝግባዎች ተዘርግተዋል። |
ሎጥም ዓይኖቹን አነሣ፤ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።
እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ይኖራል፤ እንደ ነፍስህም ፍላጎት ያጠግብሃል፤ አጥንትህንም ያለመልማል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።
አሳዳጆች ይፈሩ፤ እኔ ግን አልፈር፤ እነርሱ ይደንግጡ፤ እኔ ግን አልደንግጥ፤ ክፉንም ቀን አምጣባቸው፤ በሁለት እጥፍ ጥፋት ቀጥቅጣቸው።
ይመጣሉ፤ በጽዮንም ተራራ ደስ ይላቸዋል፤ ወደ እግዚአብሔርም በጎነት፥ ወደ እህልና ወደ ወይን ጠጅ፥ ወደ ዘይትም፥ ወደ በጎችና ወደ ላሞች ሀገርም ይሰበሰባሉ፤ ነፍሳቸውም እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፤ ከእንግዲህም ወዲህ አይራቡም።
በወንዙም አጠገብ በዳሩ ላይ በዚህና በዚያ ፍሬው የሚበላ ዛፍ ሁሉ ይበቅላል፤ ቅጠሉም አይረግፍም፤ ፍሬውም አይጐድልም፤ ውኃውም ከመቅደስ ይወጣልና በየወሩ ሁሉ የፍሬ በኵር ያገኛል፤ ፍሬውም ለመብል፥ ቅጠሉም ለመድኀኒት ይሆናል።”
“በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ተራሮች ማርን ያንጠባጥባሉ፤ ኮረብቶችም ወተትን ያፈስሳሉ፤ በይሁዳም ያሉት ፈፋዎች ሁሉ ውኃን ያጐርፋሉ፤ ከእግዚአብሔርም ቤት ምንጭ ትፈልቃለች፤ የሰኪኖንንም ሸለቆ ታጠጣለች።