የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማንም እግዚአብሔር በእርሱ እጅ ለሶርያ ደኅንነትን ስለ ሰጠ፥ በጌታው ዘንድ ታላቅና ክቡር ሰው ነበረ፤ ሰውዬውም ጽኑዕ፥ ኀያል ነበረ፤ ነገር ግን ለምጻም ነበረ።
ዘኍል 24:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አግንም ባየው ጊዜ በምሳሌ ይናገር ጀመር፤ እንዲህም አለ፦ “እግዚአብሔር ይህን ሲያደርግ አወይ ማን በሕይወት ይኖራል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ንግሩን ቀጠለ፤ “ወዮ! አምላክ ይህን ሲያደርግ ማን ይተርፋል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምሳሌውንም ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “እግዚአብሔር ይህን ባደረገ ጊዜ ወዮ! ማን በሕይወት ይኖራል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጨረሻም በለዓም የሚከተለውን የትንቢት ቃል ተናገረ፤ “በሰሜን በኩል የተሰበሰበ ይህ ሕዝብ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምሳሌውንም ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር ይህን ሲያደርግ አወይ! ማን በሕይወት ይኖራል? |
የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማንም እግዚአብሔር በእርሱ እጅ ለሶርያ ደኅንነትን ስለ ሰጠ፥ በጌታው ዘንድ ታላቅና ክቡር ሰው ነበረ፤ ሰውዬውም ጽኑዕ፥ ኀያል ነበረ፤ ነገር ግን ለምጻም ነበረ።
ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው?
በያዕቆብ ላይ ጥንቆላ የለም፤ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም፤ በየጊዜው ስለ ያዕቆብና ስለ እስራኤል፦ እግዚአብሔር ምን አደረገ? ይባላል።