ዘኍል 24:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቄኔዎናውያንንም አይቶ በምሳሌ ይናገር ጀመር፤ እንዲህም አለ፦ “ማደሪያህ የጸናች ናት፤ ጎጆህም በአንባ ላይ ተሠርቶአል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቄናውያንንም አይቶ ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤ “መኖሪያህ አስተማማኝ ነው፤ ጐጆህም በዐለት ውስጥ ተሠርቷል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቄናውያንንም አይቶ ምሳሌውን ይምስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “ማደሪያህ የጸና ነው፥ ጎጆህም በዐለት ላይ ተሠርቶአል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ቄናውያን መለስ ብሎ የሚከተለውን የትንቢት ቃል ተናገረ፦ “መኖሪያህ አስተማማኝ ቢመስልና፥ ጎጆህም በተራራው ቋጥኝ ውስጥ ቢሆን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቄናውያንምም አይቶ ምሳሌውን ይምስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ ማደሪያህ የጸና ነው፥ ጎጆህም በአምባ ላይ ተሠርቶአል፤ |
እኔም እንደምሸመግልና እንደማረጅ፥ እንደ ረዥም ዘንባባም ረዥም ዘመን እንደምኖር፥ እንደ አሸዋም ዘመኔን እንደማበዛ ዐሰብሁ።
የቄናዊው የሙሴ አማት የዮባብ ልጆችም ከዘንባባ ከተማ ተነሥተው ከዓራድ በአዜብ በኩል ወዳለው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወደ ይሁዳ ልጆች ሄደው ከሕዝቡ ጋር ተቀመጡ።
ሳኦልም ቄኔዎናውያንን፥ “ከእነርሱ ጋር እንዳላጠፋችሁ ከአማሌቃውያን መካከል ተነሥታችሁ ሂዱ፤ ከግብፅ በወጡ ጊዜ ለእስራኤል ልጆች ቸርነት አድርጋችኋልና” አላቸው። ቄኔዎናውያንም ከአማሌቃውያን መካከል ወጡ።