በለዓምም መልሶ የባላቅን አለቆች፥ “ባላቅ በቤቱ የሞላውን ወርቅና ብር ቢሰጠኝ፥ በትንሹ ወይም በትልቁ ቢሆን የአምላኬን የእግዚአብሔርን ቃል እተላለፍ ዘንድ አይቻለኝም፤
ዘኍል 24:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በለዓምም ባላቅን አለው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በለዓምም ለባላቅ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ወደ እኔ ለላክሃቸው ሰዎች እንዲህ ብዬ ነግሬአቸው አልነበረምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በለዓምም ባላቅን እንዲህ አለው፦ “አንተ ወደ እኔ ለላክሃቸው መልእክተኞችህ እንዲህ ብዬ ነግሬአቸው አልነበረምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በለዓምም እንዲህ ሲል ለባላቅ መለሰለት፦ “ወደ እኔ ልከሃቸው ለነበሩ ሰዎች፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በለዓምም ባላቅን አለው፦ ባላቅ በቤቱ የሞላውን ብርና ወርቅ ቢሰጠኝ፥ መልካሙን ወይም ክፉውን ከልቤ ለማድረግ እግዚአብሔርን ቃል እተላለፍ ዘንድ አይቻለኝም፤ እግዚአብሔር የተናገረውን እርሱን እናገራለሁ ብዬ ወደ እኔ ለላክሃቸው መልእክተኞችህ አልተናገርኋቸውምን? |
በለዓምም መልሶ የባላቅን አለቆች፥ “ባላቅ በቤቱ የሞላውን ወርቅና ብር ቢሰጠኝ፥ በትንሹ ወይም በትልቁ ቢሆን የአምላኬን የእግዚአብሔርን ቃል እተላለፍ ዘንድ አይቻለኝም፤
በለዓምም ባላቅን፥ “እነሆ፥ ወደ አንተ መጥቼአለሁ፤ አሁን አንዳችን ነገር ለመናገር እችላለሁን? እግዚአብሔር በአፌ የሚያደርገውን ቃል እርሱን እናገራለሁ” አለው።
እነሆም፥ ፈጽመህ መረቅሃቸው፤ ይህ ሦስተኛህ ነው፤ አሁንም እንግዲህ ወደ ስፍራህ ሂድ፤ እኔ አከብርሃለሁ ብዬ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን እነሆ፥ ክብርህን ከለከለ።”