ዘኍል 23:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እርሱም ተመለሰ፤ እነሆም፥ እርሱና የሞዓብ አለቆች ሁሉ በመሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ ወደ እርሱ መጣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ተመልሶ ሲሄድ ባላቅን ከመላው የሞዓብ አለቆች ጋራ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አገኘው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ባላቅም ተመለሰ፥ እነሆም፥ እርሱና የሞዓብ ሹማምንት ሁሉ በሚቃጠለው መሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ተመልሶ ሲሄድ ባላቅ ከሞአብ መሪዎች ሁሉ ጋር ሆኖ በዚያው በሚቃጠለው መሥዋዕት አጠገብ እንደ ቆመ አገኘው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እርሱም ተመለሰ፥ እነሆም፥ እርሱና የሞዓብ አለቆች ሁሉ በመሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር። |
በምሳሌም ይናገር ጀመር፤ እንዲህም አለ፦ “የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ከምሥራቅ ተራሮች፤ ከሜስጴጦምያ ጠርቶ አመጣኝ፤ ና፥ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፥ እስራኤልን ተጣላልኝ” ብሎ።