ወርቁንና ብሩን ከኮሮጆ የሚያወጡና በሚዛን የሚመዝኑ እነርሱ አንጥረኛውን ይቀጥራሉ፤ እርሱም ጣዖት አድርጎ ይሠራዋል፤ ለዚያም ይጐነበሱለታል፤ ይሰግዱለትማል።
ዘኍል 23:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሜዳ ወደ ተገነባ ግንብ ራስ ላይም ወሰደው፤ አዞረውም፤ ሰባትም መሠዊያዎች ሠራ፤ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈን፥ አንድም አውራ በግ አሳረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም በፈስጋ ተራራ ጫፍ ላይ ወዳለው ወደ ጾፊም ሜዳ ወሰደው፤ እዚያም ሰባት መሠዊያ ሠርቶ በእያንዳንዱ ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ ሠዋ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ጾፊምም ሜዳ ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ ላይ ወሰደው፤ ሰባትም መሠዊያዎች ሠራ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈን አንድም አውራ በግ አሳረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በፒስጋ ተራራ ጫፍ ላይ ወደሚገኘው ወደ ጾፊም መስክ ወሰደው፤ እዚያም ሰባት መሠዊያዎችን ሠርቶ በእያንዳንዱ ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ ሠዋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ጾፊምም ሜዳ ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ ላይ ወሰደው፤ ሰባትም መሠዊያዎች ሠራ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈን አንድም አውራ በግ አሳረገ። |
ወርቁንና ብሩን ከኮሮጆ የሚያወጡና በሚዛን የሚመዝኑ እነርሱ አንጥረኛውን ይቀጥራሉ፤ እርሱም ጣዖት አድርጎ ይሠራዋል፤ ለዚያም ይጐነበሱለታል፤ ይሰግዱለትማል።
ባላቅም፥ “በዚያ እነርሱን ወደማታይበት ወደ ሌላ ቦታ እባክህ፥ ከእኔ ጋር ና፤ ከእነርሱ አንዱን ወገን ብቻ ታያለህ፤ ሁሉን ግን አታይም፤ በዚያም እነርሱን ርገምልኝ” አለው።
ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርምና ወደ ተራራው ራስ ውጣ፤ ዐይንህንም ወደ ባሕር ወደ መስዕም፥ ወደ አዜብም ወደ ምሥራቅም አንሥተህ በዐይንህ ተመልከት።
ሙሴም ከሞዓብ ሜዳ በኢያሪኮ ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ወደ ፈስጋ ራስ ወጣ፤ እግዚአብሔርም እስከ ዳን ድረስ ያለውን የገለዓድን ምድር አሳየው፤